ኢትዮጵያ ሕገ-ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ላይ ያነጣጠረ ጠንካራ ሕግ ልታፀድቅ ነው

ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ሕገ-ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ላይ ያነጣጠረ ጠንካራ ሕግ ልታፀድቅ ነው

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ላለፉት 18 ዓመታት ሲሠራበት የቆየውንና ክፍተቶች ያሉበትን ሕግ በአዲስና ጥብቅ ሕግ ለመተካት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

አዲሱ ሕግ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያስችልና ሕገ-ወጥ ዝውውሩን "አክሳሪ" የሚያደርግ ጠንካራ ቅጣቶችን የያዘ ነው ተብሏል።

ረቂቅ ሕጉ የጎረቤት ሀገራትን በተለይም የኬንያን ተሞክሮ መነሻ ያደረገ ሲሆን ሲጸድቅ በኢትዮጵያ የዱር እንስሳትና ውጤቶቻቸውን ከሕገ-ወጥ ዝውውር ለመታደግ ትልቅ አቅም ይሆናል መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0