ኢትዮጵያ ስንዴ ከውጭ ማስገባቷን በማቆሟ 1 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሏ ተገለፀ
17:39 08.04.2026 (የተሻሻለ: 17:44 08.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ስንዴ ከውጭ ማስገባቷን በማቆሟ 1 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሏ ተገለፀ
ሀገሪቱ ላለፉት ሦስት ዓመታት ስንዴን በሀገር ውስጥ ምርት በማምረት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ ማስቀረቷን የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
በ2013 ዓ.ም 27 ሚሊዮን ደርሶ የነበረው የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ወደ 2 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱን ኮሚሽነር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ገልፀዋል።
ሀገሪቱ ለድንገተኛ አደጋዎች 20 ሚሊዮን ኩንታል የመጠባበቂያ እህል እንደሚያስፈልጋትና ይህንን ለሟሟላት በ250 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ እህሉን ለማልማት እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ ክልሎች የሚገጥሟቸውን የምግብ ፍላጎቶች በራሳቸው አቅም እየሸፈኑ ይገኛሉ ማለታቸውንም የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X