ዚምባብዌ ለ8 የሊቲየም እና የብረት ማዕድን ቁፋሮ ቦታዎች የልዩ ኢኮኖሚ ቀጣና ደረጃ ለመስጠት ማቀዷ ተገለፀ
16:52 08.04.2026 (የተሻሻለ: 17:27 08.04.2026)

ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ ለ8 የሊቲየም እና የብረት ማዕድን ቁፋሮ ቦታዎች የልዩ ኢኮኖሚ ቀጣና ደረጃ ለመስጠት ማቀዷ ተገለፀ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔን እየተጠባበቀ ያለው ይህ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የጋራ የውሳኔ ሃሳብ፤ ሊቲየም እና ብረት በብዛት የሚገኝባቸውን የማዕድን ቦታዎች ወደ ኢንዱስትሪ ማዕከልነት ለመቀየር ያለመ ነው። ይህም ከማዕድን ቁፋሮ ወደ ሀገር ውስጥ ማቀነባበር የሚደረገው ሽግግር ምልክት መሆኑን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
እንደ የዚምባቡዌ የንግድና ኢንዱስትሪሚኒስትር ማንጋሊሶ ንድሎቩ ገለጻ፣ ይህ እርምጃ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል፦
◻ የቀረጥ እፎይታ፣
◻ የተቀላጠፉ የአሠራር ደንቦች፣
◻ ጥሬ ማዕድናትን ወደ ውጭ መላክን ለመቀነስ የሚያስችሉ የሀገር ውስጥ ማቀነባበሪያ መሠረተ ልማቶች።
ይህ ተነሳሽነት መንግሥት ጥሬ ሊቲየም እና ሌሎች ቁልፍ ማዕድናትን ወደ ውጭ መላክ ካገደ በኋላ የመጣ ሲሆን ዚምባብዌ የማዕድን ውጤቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ለመጨመር የምታደርገውን ጥረት የሚያጠናክር ነው።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X