ኢትዮጵያ የተፋሰሱ ሀገራት በሕዳሴው ግድብ የሚገኘውን የተረጋጋ የውኃ ፍሰት በመጠቀም የመስኖ ልማታቸውን እንዲያስፋፉ ጥሪ አቀረበች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የተፋሰሱ ሀገራት በሕዳሴው ግድብ የሚገኘውን የተረጋጋ የውኃ ፍሰት በመጠቀም የመስኖ ልማታቸውን እንዲያስፋፉ ጥሪ አቀረበች

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ያለምንም ወጪ ከጎርፍ አደጋ ከመታደጉ ባለፈ፤ ዓመቱን ሙሉ የተረጋጋ የውኃ ፍሰት እንዲኖር ማስቻሉን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

"ኢትዮጵያ ግብፅን ልትጎዳ ነው" የሚለው ፕሮፓጋንዳ በተግባር ሐሰት መሆኑ ቢረጋገጥም፤ ግብፅ አሁንም የተሳሳቱ መረጃዎችን የማሰራጨት ተግባሯን ስላልተወች የውኃ ሀብት ባለሙያዎች፣ ምሁራንና የሚዲያ አካላት እውነታውን ለዓለም የማሳወቅ ኃላፊነት አለባቸው ሲሉ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ግድቡን ለቀጣናው ሀገራት የጋራ ብልጽግና እንጂ ሌሎችን ለመጉዳት እንደማታውልም በድጋሚ አረጋግጣለች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0