አፍሪካ የራሷን የሰብዓዊ ድጋፍ ተቋም ልትመሰርት ይገባል - የዛምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት

ሰብስክራይብ

አፍሪካ የራሷን የሰብዓዊ ድጋፍ ተቋም ልትመሰርት ይገባል - የዛምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት

ይህ የተባለው በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም አኅጉራዊ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ የቪዲዮ መልዕክት ያስተላለፉት የዛምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሙታሌ ናሉማንጎ፤ “የኅብረቱ የአፍሪካ የአደጋ ስጋት አቅም ኤጀንሲ ላለፉት 14 ዓመታት በለጋሽ ሃገራት ሲደገፍ ቆየሰቷል። ይህ ሊያበቃ ይገባዋል። በዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ አፍሪካ በርካታ ችግሮችን ለመጋፈጥ ተገዳለች። ይህም አኅጉሪቱ የራሷን ተቋም ትገነባ ዘንድ ማንቂያ ነው” ብለዋል።

የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም በበኩላቸው፤ "የአፍሪካ ሀገራት በአኅጉሪቱ የአደጋ ዝግጁነትን ለማጠናከር፣ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በትብብር መሥራት እንዳለባቸው” ለስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ተናግረዋል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባኤ የአፍሪካ ሀገራት የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነታቸውን ማረጋገጥ በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ ይመክራል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0