"የሆርሙዝ ወሽመጥ መከፈት ለአየር መንገዱ ትልቅ እፎይታ ነው" - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

ሰብስክራይብ

"የሆርሙዝ ወሽመጥ መከፈት ለአየር መንገዱ ትልቅ እፎይታ ነው" - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ወደ 11 ከተሞች የሚደረጉ በረራዎችን እንዳቋረጠና 101 በረራዎች ተሰርዘው እንደነበር አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱን 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

አየር መንገዱ በመንገደኞች ቁጥር መቀነስ፣ በነዳጅ አቅርቦት መስተጓጐል እና በነዳጅ ዋጋ መናር መፈተኑንም አክለዋል።

ሆኖም “ባለን ፈተናዎችን የማለፍ ልምድ እና ጠንካራ የውስጥ አቅም ተቋቁመን አልፈነዋል” ማለታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

ነዳጅ ጅዳን፣ መስካትን፣ ጅቡቲንና ካምፓላን ከመሳሰሉ ከተሞችና ከጎረቤት ሀገራት በመቅዳት፣ ከተለያዩ አማራጮች በመግዛት እና የጉዞ ዋጋን ጨምሮ በተወሰኑ አሠራሮች መጠነኛ ማሻሻያዎችን በማድረግ ችግሩ መታለፉንም አብራርተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0