በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈለገው አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

ሰብስክራይብ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈለገው አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ

‍ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር ባደረገው ኦፕሬሽን፤ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ያዘዋወረው ይትባረክ ዳዊትን (ክብሮም) ከ9 ግብረአበሮቹ ጋር በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል።

ተጠርጣሪው ከ100 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት እና ከ50 በላይ ሴቶች መደፈር ምክንያት መሆኑ በምርመራ ተረጋግጧል ተብሏል።

በኤርትራ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ እና አውሮፓ ሀገራት እንደ ክብሮም፣ ሙኒር እና አድሀኖም ያሉ የተለያዩ ሀሰተኛ ስሞችን ሲጠቀም መቆየቱ ተገልጿል።

ቡድኑ በሊቢያ ውስጥ አምስት የማገቻ መጋዘኖች እንዳሉት እና ከ3 ቢሊዮን በላይ ብር በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያንቀሳቅስ እንደነበር ፖሊስ በመግለጫው ጠቅሷል።

‍ ፖሊስ በ9 ሀገራት የሚገኙ ተጎጂዎችን ምስክርነት በመቀበል ምርመራውን አጠናቆ ለዓቃቢ ሕግ መላኩን አመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0