የባብ ኤል-ማንደብ የመዘጋት ስጋት አሜሪካ ከኢራን ጋር እንድትደራደር እየገፋት መሆኑ ተገለፀ

ባብ ኤል-ማንደብ
ባብ ኤል-ማንደብ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.04.2026
ሰብስክራይብ
የባብ ኤል-ማንደብ የመዘጋት ስጋት አሜሪካ ከኢራን ጋር እንድትደራደር እየገፋት መሆኑ ተገለፀ

በአፍሪካ እና በአረብ ባሕረ ገብ መሬት መካከል ያለው ወሳኝ የባሕር መስመር የተጋረጠበት የመዘጋት ስጋት እንዲሁም በኢስፋሃን የተከሰከሰውን የጦር አውሮፕላን ፓይለት ለማዳን አሜሪካ ያደረገችው ሙከራ ባለመሳካቱ፤ ዋሽንግተን ከቴህራን ጋር ንግግር ለመጀመር መገደዷን የሊባኖስ መገናኛ ብዙኃን የኢራን ምንጮችን ጠቅሰው ዘግበዋል።


"የትራምፕ አስተዳደር ስልታዊው የባብ ኤል-ማንደብ ሰርጥ የመዘጋት ስጋትን በተለይም ከተወሰኑ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች አኳያ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተመለከተው ይገኛል" ሲሉ ምንጩ ገልጸዋል።


ዋሽንግተን በምድር ጉልህ ውጤት የማምጣት ወይም በባሕር ኢራንን በተሳካ ሁኔታ የመጋፈጥ ተስፋ እንደሌላት ተገንዝባለች ሲሉም ምንጩ አክለዋል።

አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21 በኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት ውድመትና የሲቪል ሰዎች ግድያ አስከትለዋል። በምላሹ ኢራን በእስራኤል ግዛት እና በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ሀብቶች ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰንዝራለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0