ሶማሊያ ከቱርክ ጋር በመተባበር የመጀመሪያውን የባሕር ነዳጅ ቁፋሮ ልትጀምር መሆኑ ተነገረ

ሶማሊያ ቱርክ
ሶማሊያ ቱርክ  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.04.2026
ሰብስክራይብ
ሶማሊያ ከቱርክ ጋር በመተባበር የመጀመሪያውን የባሕር ነዳጅ ቁፋሮ ልትጀምር መሆኑ ተነገረ

ቻሪ ቤይ የተባለችውና በቱርክ መንግሥት ባለቤትነት ስር የምትገኘው የቁፋሮ መርከብ፤ በአረብ ባሕር ወለል የፍለጋ ስራ ለመጀመር አርብ ሶማሊያ ጠረፍ ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።

ቁፋሮው በ2024 በተፈረመው የምርት ክፍፍል ስምምነት መሰረት በቱርክ ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን አማካኝነት እንደሚከናወን ተገልጿል።

የሶማሊያ የነዳጅ ሚኒስትር ዳሂር ሽሬ "በባሕር ኢነርጂ እና በቢሊዮን በርሜል ከሚገመት ክምችት ለመጠቀም በምናደርገው ጥረት አዲስና ታሪካዊ ምዕራፍ" ሲሉ ገልፀውታል።


ሚኒስትሩ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፤ "ሶማሊያ የተፈጥሮ ሀብት ዘርፏን በግልጽነት፣ በተጠያቂነት እና ከዓለም አቀፍ አሠራር ጋር በተጣጣመ መልኩ በማሳደግ ለሀገራዊ ብልጽግና እና ለሕዝባችን ደህንነት ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ለማስቻል ቁርጠኛ ናት" ብለዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0