የዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎች በግብዓት ራሳቸውን እንዲችሉ ለስንዴ ምርት የሚሆን እርሻ መሬት እያዘጋጀሁ ነው - የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት
14:53 07.04.2026 (የተሻሻለ: 14:54 07.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የዳቦና ዱቄት ፋብሪካዎች በግብዓት ራሳቸውን እንዲችሉ ለስንዴ ምርት የሚሆን እርሻ መሬት እያዘጋጀሁ ነው - የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት
ፅ/ቤቱ በቀን እስከ 300 ሺህ ዳቦ እና 420 ኩንታል ዱቄት የማምረት አቅም ያላቸው 14 የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካዎችን መገንባቱን አስታውቋል፡፡
ለሰመራ ብርሀን ዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ ከተዘጋጀው 500 ሄክታር መሬት ውስጥ በመጀመሪያው ዙር 100 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ በመዝራት 2000 ኩንታል የስንዴ ምርት ለማምረት ተችሏል፡፡
ይህ ተነሳሽነት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት እና የሀገር ውስጥ ምርት ስርዓትን ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።
ቪዲዮው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም የአሶሳ ዱቄት እና ዳቦ ፋብሪካን ሲያስመርቁ ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X