- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል።አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

አፍሪካን የመበየን አባዜ:- የምዕራባውያን የጥናት ተቋማት የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መሣሪያነት

አፍሪካን የመበየን አባዜ:- የምዕራባውያን የጥናት ተቋማት የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መሣሪያነት
ሰብስክራይብ

“የምዕራባውያን ስረዓቶች በአመፃ የታጀቡ ናቸው። ዛሬ በዓለም ዙሪያ ያሉትን ብዙ ግጭቶች ብንመለከት፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የምዕራባውያን እጅ አለበት። ይህንን ሁኔታ በተመሳሳይ ቀውስ ውስጥ ሁለት ሚና ይዞ መገኘት እለዋለሁ። ችግር ፈጣሪዎች ለችግሩ ስም ያወጡለታል፣ ለፈጠሩት ችግር ደግሞ መፍትሄ ፈጣሪዎች ሆነው ይመጣሉ። ይህ ምዕራባውያን መገለጫ ነው” ሲሉ በደቡብ አፍሪካው ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሩ።

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን አፍሪካ የምትታይበትን እይታ የሚቀርፀው ማነው ስንል እንተይቃለን። ለዚህም በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የታቦ ምቤኪ የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የድህረ ምረቃ ምርምር ባልደረባ ቺዶካሼ ንዬሬን (ዶ/ር) አነጋግረናል። ሁለተኛ ጉዳያችን ደግሞ 10ኛው የኢትዮ ጤና ኤግዚቢሽን እና ኮንግረስ 2026 ላይ የሚያተኩር ይሆናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0