በወሳኝ የባሕር መተላለፊያዎች ላይ እያጋጠሙ ያሉ አሁናዊ ፈተናዎች የጋራ የማሪታይም አስተዳደር አስፈላጊነትን እንደሚያሳዩ ተገለጸ

የማሪታይም አስተዳደር
የማሪታይም አስተዳደር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.04.2026
ሰብስክራይብ
በወሳኝ የባሕር መተላለፊያዎች ላይ እያጋጠሙ ያሉ አሁናዊ ፈተናዎች የጋራ የማሪታይም አስተዳደር አስፈላጊነትን እንደሚያሳዩ ተገለጸ

ይህ የተባለው ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው 4ኛው የቀይ ባሕር እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ ጉባኤ (RESGA) ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ፤ “ፈተናዎቹ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ አንገብጋቢነት ብቻ ሳይሆን ጥያቄው ወቅታዊና ፍትሐዊ እንደሆነ የሚያሳዩ ናቸው” ሲሉ በጉባኤው መክፈቻ ላይ መናገራቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ ገልጿል።

ሆኖም የጋራ የማሪታይም አስተዳደሩ በጥቂት ወይም በሌሎች የውጭ አካላት ሊወሰን እንደማይገባው አሳስበዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ኢንሲቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃፋር በድሩ በበኩላቸው፤ ቀይ ባሕር የትበብር እንጂ የልዩነትና የፉክክር ምንጭ ሊሆን እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0