የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት ለአማራ ክልል 25 ሺህ የፀሐይ ብርሃን መሣሪያዎችን አዳረሰ

የፀሐይ ብርሃን መሣሪያዎች
 የፀሐይ ብርሃን መሣሪያዎች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.04.2026
ሰብስክራይብ
የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለፉት ስድስት ወራት ለአማራ ክልል 25 ሺህ የፀሐይ ብርሃን መሣሪያዎችን አዳረሰ

አቅርቦቱ በዋናነት ከብሔራዊ የኃይል መስመር ርቀው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በቀጣይ ከ5 ዋት እስከ 50 ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ተጨማሪ 45 ሺህ የቤተሰብ የፀሐይ ኃይል መሣሪያዎችን ለማሰራጨት መታቀዱን የውኃና ኢነርጂሚኒስትር ዴኤ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ ተናግረዋል።

አክለውም በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን በ2022 ዓ.ም ወደ 75 በመቶ ለማድረስ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል (ንፋስ፣ ፀሐይ፣ ውኃ እና ጂኦተርማል) የማመንጨት አቅም 150 ጊጋ ዋት ቢሆንም፤ እስካሁን ጥቅም ላይ የዋለው 9.5 ጊጋዋት ብቻ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0