የአፍሪካ ሀገራት እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ለመቋቋም ምን ዓይነት እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው?
11:35 06.04.2026 (የተሻሻለ: 12:03 06.04.2026)

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ለመቋቋም ምን ዓይነት እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው?
በመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ሳቢያ እየጨመረ ከመጣው ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ሸማቾችንና ቁልፍ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለመታደግ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የተለያዩ እርምጃዎችን መተግበር ጀምረዋል።
◻ ጋምቢያ፦ እንደ የሀገሪቱ የነዳጅ ሚኒስቴር መግለጫ ከሆነ የጋምቢያ መንግሥት የናፍጣ ዋጋን በ24 በመቶ ወደ 1.29 ዶላር፤ የቤንዚን ዋጋን ደግሞ በ3 በመቶ ወደ 1.32 ዶላር በመቀነስ የነዳጅ ወጪን ለመደጎም ወስኗል።
◻ ደቡብ አፍሪካ፦ የማዕድንና ነዳጅ ሀብት ሚኒስቴር ወርሃዊ የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ማድረጉንና የነዳጅ ቀረጥ ላይ በሊትር 0.17 ዶላር አካባቢ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።
◻ ናሚቢያ፦ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሸማቾችን ከሚንረው የነዳጅ ዋጋ ለመጠበቅ ቢያንስ ለሦስት ወራት የነዳጅ ቀረጥን በ50 በመቶ መቀነሱን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
◻ ኢትዮጵያ፦ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት ሳቢያ የሀገር ውስጥ የነዳጅ ዋጋን በአንፃራዊነት ለማረጋጋት መንግሥት ድጎማ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
◻ ዛምቢያ፦ መንግሥት ከሚያዝያ 1 ቀን ጀምሮ ለሦስት ወራት የተጨማሪ እሴት ታክስን ነፃ በማድረግ፤ የኤክሳይዝ ታክስን አንስቷል።
◻ ዚምባብዌ፦ ኢኮኖሚው በውጫዊ ቀውሶች እንዳይናጋ ለመከላከል በናፍጣ ላይ የሚጣሉ ታክሶች ለጊዜው እንዲነሱ መንግሥት መወሰኑን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
◻ ሞሮኮ፦ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት መስተጓጎል ሳቢያ የቤተሰቦች የጋዝ ዋጋ እንዳይለወጥ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ድጎማ እንዲቀጥል ማድረጉን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ጠቁመዋል።
◻ ኬንያ፦ መንግሥት የነዳጅ ልማት ቀረጥን በመጠቀም የዋጋ ጣሪያ ሊያወጣ መሆኑን የብሔራዊ ግምጃ ቤት ጸሐፊ ጆን ምባዲ አስታውቀዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X