በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት ለኢራን እና ለአፍሪካ የሚቀርበውን ሰብአዊ እርዳታ እያስተጓጎለ መሆኑን የረድኤት ተቋማት ገለጹ
18:20 05.04.2026 (የተሻሻለ: 18:28 05.04.2026)

ሰብስክራይብ
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት ለኢራን እና ለአፍሪካ የሚቀርበውን ሰብአዊ እርዳታ እያስተጓጎለ መሆኑን የረድኤት ተቋማት ገለጹ
እየተካሄደ ያለው ግጭት ወደ ኢራን እና አፍሪካ ሀገራት የሚላኩ የክትባት እና የእርዳታ ጭነቶችን እያስተጓጎለ መሆኑን፣ ይህም ለከፍተኛ ወጪ እና ለረጅም የመድረሻ ጊዜ ምክንያት እንደሆነ የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የዩኒሴፍ እና የ"ሴቭ ዘ ችልድረን" መረጃን በመጥቀስ ዘግበዋል።
እንደ ናይጄሪያ እና ኢራን ላሉ ሀገራት በቱርክ በኩል የሚጓጓዙ የክትባት አቅርቦቶች አሁን ላይ የወጪ መጠናቸው በ20 በመቶ የጨመረ ሲሆን፣ የመድረሻ ጊዜያቸውም በአስር ቀናት መራዘሙን የዩኒሴፍ ዓለም አቀፍ የትራንስፖርት ኃላፊ ገልጸዋል።
ሴቭ ዘ ችልድረን ባጋራው መረጃ፣ ወደ ሱዳን ለሚላኩ ቁሳቁሶች እንደ አማራጭ ጥቅም ላይ የሚውለው የቀይ ባህር መስመር ተጨማሪ አስር ቀናትን እና የ25 በመቶ የዋጋ ጭማሪን አስከትሏል።
አሜሪካ እና እስራኤል በየካቲት 21 በኢራን ላይ ጥቃት የሰነዘሩ ሲሆን፣ ቴህራንም በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የእስራኤል እና የአሜሪካ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዷንና የሆርሙዝ ወሽመጥን ሙሉ በሙሉ መዝጋቷ ይታወሳል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X