የሞስኮ የንግድ ልዑክ በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የኢንቨስትመንት ዕድሎችን አጠና
13:15 05.04.2026 (የተሻሻለ: 13:27 05.04.2026)

ሰብስክራይብ
የሞስኮ የንግድ ልዑክ በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የኢንቨስትመንት ዕድሎችን አጠና
ከ13 በላይ የሞስኮ ኩባንያዎችን ያቀፈ የሩሲያ የቢዝነስ ልዑካን ቡድን በቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ እና መንግስት ያዘጋጀውን ማበረታቻ ገምግሟል።
ልዑኩ በተለይም በጤና፣ በፋርማሲዩቲካል፣ በሃይ-ቴክ እና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ሀብትና እውቀቱን ለማፍሰስ ያለውን ዝግጁነት መግለጹን የኢትዮጵያ የኢንስዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገልጿል።
በተጨማሪም በዞኑ ውስጥ በምርት ላይ ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር በመወያየት በተግባር ያለውን የሥራ ሂደት የተመለከተ ሲሆን፣ ይህም የሩሲያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ መነሻ እንደሚሆን ተመልክቷል።
ልዑካኑ በመድኃኒት፣ በሕክምና ቴክኖሎጂዎች ምርት እና አቅርቦት ላይ ያተኮረው የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ንግድ ፎረም እና ዐውደ ርዕይ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X