የካሜሩን ፓርላማ የምክትል ፕሬዝዳንት የሥራ መደብ እንዲፈጠር የቀረበውን የሕግ ማሻሻያ አጸደቀ

ሰብስክራይብ

የካሜሩን ፓርላማ የምክትል ፕሬዝዳንት የሥራ መደብ እንዲፈጠር የቀረበውን የሕግ ማሻሻያ አጸደቀ

​የአገሪቱ ፓርላማ ሁለቱ ምክር ቤቶች ባደረጉት የጋራ ስብሰባ የምክትል ፕሬዝዳንት የሥራ መደብን የሚያስተዋውቅ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ማፅደቁን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

​በስብሰባው ላይ የተገኙት 222 እንደራሴዎች እና ሴናተሮች ለማሻሻያው እጅግ ከፍተኛ ድጋፍ የሰጡ ሲሆን፣ የድጋፍ ድምፁ እንደሚከተለው ተመዝግቧል፡፡

​🟩 200 ድጋፍ፣

🟥 18 ተቃውሞ እና

🟨 4 ድምጸ ተዓቅቦ።

​​የሕግ ረቂቁ እንዲጸድቅ ለፕሬዝዳንት ፖል ቢያ ለፊርማ ቀርቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0