ኢራን በ95ኛው ዘመቻ እውነተኛ ቃል ኪዳን 4፣ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካን እና የእስራኤልን ኢላማዎች መታች - የኢራን አብዮታዊ ዘብ
20:16 04.04.2026 (የተሻሻለ: 20:24 04.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢራን በ95ኛው ዘመቻ እውነተኛ ቃል ኪዳን 4፣ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካን እና የእስራኤልን ኢላማዎች መታች - የኢራን አብዮታዊ ዘብ
የኢራን ጦር ኃይሎች በኩዌት፣ ባህሬን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና እስራኤል ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ እና የእስራኤል ኢላማዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች የኢራን አብዮታዊ ዘብንን መግለጫ ዋቢ አድርገው ዘግበዋል።
ጥቃቱ በኩዌት የሚገኙ የአሜሪካ ሂማርስ ባለብዙ ሮኬት ማስወንጨፊያዎችን፣ በባህሬን የሚገኝ የፓትሪዮት ሚሳኤል ስርዓትን፣ የአሜሪካ የሚሳኤል ጣቢያዎችን፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚገኝ የአሜሪካ መኮንኖች የዕዝ ማዕከል እና በኤምሬቶች ውስጥ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ ላይ የሚንቀሳቀሰውን ኦራክል ኩባንያን መምታቱን ዘቡ ገልጿል።
በተጨማሪም ቴል አቪቭ እና ፔታ ቲክቫን ጨምሮ በተለያዩ የእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ስፍራዎች የጥቃቱ ኢላማ መሆናቸውን የኢራን አብዮታዊ ዘብ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X