ብርቅዬውን ቋንቋ ማስተዋወቅ - የሩሲያ ዩኒቨርሲቲ የስዋሂሊ ባሕል ቀንን አከበረ

ሰብስክራይብ
ብርቅዬውን ቋንቋ ማስተዋወቅ - የሩሲያ ዩኒቨርሲቲ የስዋሂሊ ባሕል ቀንን አከበረ

​በሩሲያ የሕዝቦች ወዳጅነት ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት በትናንትናው ዕለት በተከበረው ደመቅ ያለ የስዋሂሊ ባሕል ቀን ላይ ከ13 ሀገራት የተውጣጡ ከ300 በላይ ተሳታፊዎች መገኘታቸውን አዘጋጆቹ ሁነቱን ለታደመው የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ገልጸዋል።

​የዝግጅቱ ዓላማ የስዋሂሊ ቋንቋ እና ባሕል በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና በሰፊው ሕዝብ ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ፣ በሩሲያ እና በምሥራቅ አፍሪካ አገራት መካከል ያለውን ሰብአዊ ግንኙነት ማጠናከር፣ እንዲሁም ለባህላዊ ውይይት ንቁ መድረክ መፍጠር ነው።

አዝናኝና አስተማሪ የነበረው ባህላዊ መርሃ ግብር የሚከተሉትን አካቷል፦

🟠 የምሥራቅ አፍሪካ አገራት መጻሕፍት፣ ፎቶግራፎች እና ቅርሶች ዐውደ ርዕይ፤

🟠 በስዋሂሊኛ የቀረቡ የግጥም ንባብ እና የሙዚቃ ክዋኔዎች፤

🟠 በሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው፣ የእስያ እና አፍሪካ አገራት ተቋም (አይኤኤስ)፣ የሞስኮ መንግሥታዊ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተቋም፣ የሩሲያ የሕዝቦች ወዳጅነት ዩኒቨርሲቲ እና የሩሲያ መንግሥታዊ የሰብአዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በሚማሩ ተማሪዎች የተሰሩ የአፍሪካ ጥናቶች መድረኩ ላይ ቀርበዋል።

​የስዋሂሊ ባህል ቀን በማኅበራዊ የትስስር ገፆች ላይ እጅግ ሞቅ ያለ እና አበረታች አስተያየቶችን አስተናግዷል።

የክብር እንግዶችን ንግግር እና አፍሪካውያን ተማሪዎች በሩሲያ ስላላቸው የትምህርት ቆይታ የሰጡትን አስተያየት ለማየት የስፑትኒክን ቪዲዮ ይመልከቱ።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0