ኢትዮ ቴሌኮም አራተኛውን የእጅግ ፈጣን ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ በአዳማ ከተማ ሥራ አስጀመረ

ሰብስክራይብ

ኢትዮ ቴሌኮም አራተኛውን የእጅግ ፈጣን ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ በአዳማ ከተማ ሥራ አስጀመረ

ይህ ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ በኩባንያው የተገነባዉ የኃይል መሙያ በአዳማ ከተማ ደራርቱ አደባባይ የሚገኝ ሲሆን በአንድ ጊዜ 12 እጅግ በጣም ፈጣን መሙያዎችን ያካተተ መሆኑ ኩባንያው ባጋራው መግለጫ አሳውቋል።

ኩባንያው ቀደም ሲል በአንድ ጊዜ 48 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችሉ ጣቢያዎችን ወደ ሥራ ማስገባቱን አስታውሷል፡፡ ከየካቲት 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከ284 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች፣ 7,159,066.88 ኪሎ ዋት ኃይል መሙላት ስለመቻሉ ነው ኢትዮ ቴሌኮም የገለጸው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0