የአፍሪካ ሕብረት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምን ለማስፈን የቀረበውን የቻይና-ፓኪስታን ተነሳሽነት በበጎ ተቀበለው

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሕብረት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምን ለማስፈን የቀረበውን የቻይና-ፓኪስታን ተነሳሽነት በበጎ ተቀበለው

​ባለአምስት ነጥብ የሰላም ተነሳሽነቱ ውጥረቶችን ለመቀነስ እንዲሁም ለግጭቱ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለማምጣት ሊረዳ እንደሚችል የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ገልጸዋል።

"ተነሳሽነቱ በአስቸኳይ ግጭቶችን ማቆም፣ የሲቪሎችን ደህንነት መጠበቅ፣ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ሕጎችን ማክበር እና የባህር ላይ ደህንነትን ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ማድረጉ አሁን ያለውን ቀውስ ለመግታት የሚያስፈልጉ ቁልፍ ጉዳዮችን ያንጸባርቃል" ሲሉ ሊቀመንበሩ አፅንኦት ተሰጥተዋል።

​ ሊቀመንበሩ ሁሉም  በግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች በውይይት እና በድርድር ዘላቂ መፍትሄ በማግኘት ዓለም አቀፍ ደህንነትን፣ መረጋጋትን እና ሰላምን እንዲያስጠብቁ አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0