ኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ማስተናገዷ ዓለም አቀፍ እውቅናን አስገኝቶላታል - የኢትዮጵያ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን ማስተናገዷ ዓለም አቀፍ እውቅናን አስገኝቶላታል - የኢትዮጵያ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

የኢትዮጵያ “ክፍት በር” የስደተኞች ፖሊሲ ሀገሪቱ ቀዳሚ ሰብዓዊ አስተናጋጅ በመሆን ያላትን ዓለም አቀፍ ዝና እያጠናከረው መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሀሰን ለአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።

​ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም፣ የኢትዮጵያ የስደተኞች ስትራቴጂ ከለላ በመስጠት ላይ ብቻ ሳይወሰን ስደተኞች ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር እንዲዋሃዱ እና የትምህርት፣ የጤና እንክብካቤ፣ የምግብ እርዳታ እንዲሁም የሥራ ዕድሎችን እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ስደተኞች በመቀበል ከአፍሪካ ከኡጋንዳ በመቀጠል ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0