ሞሮኮ በ2026 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 4.3 ሚሊዮን ቱሪስቶችን አስተናገደች፤ ካለፈው ዓመት የ7% ጭማሪ አለው - የቱሪዝም ሚኒስቴር
11:43 04.04.2026 (የተሻሻለ: 12:39 04.04.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
ሞሮኮ በ2026 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 4.3 ሚሊዮን ቱሪስቶችን አስተናገደች፤ ካለፈው ዓመት የ7% ጭማሪ አለው - የቱሪዝም ሚኒስቴር
ሚኒስቴሩ በመግለጫዉ እንዳስታወቀው፣ በሞሮኮ የቱሪስቶች ቁጥር በመጋቢት ወር በ18 በመቶ የጨመረ ሲሆን ለዚህም እንደ ምክንያት የተጠቀሱት፦
🟠 የተሻሻለ የአየር ትራንስፖርት ትስስር፣
🟠 የተለያዩ የቱሪስት ምንጭ ገበያዎች መኖራቸው እና
🟠ማራኪ እና የተሻሻሉ የቱሪዝም አገልግሎቶች ናቸው።
የውጭ ምንዛሪ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፥ እስከ መጋቢት ወር መጀመሪያ ድረስ ከቱሪዝም የተገኘው ገቢ 2.3 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ22.2 በመቶ እድገት አሳይቷል።
ሀገሪቱ እ.ኤ.አ. በ2030 ከስፔን እና ከፖርቱጋል ጋር በመሆን የፊፋ የዓለም ዋንጫን በጋራ ስታስተናግድ 26 ሚሊዮን ጎብኚዎችን ለመሳብ አልማለች።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X