የአፍሪካ ባንኮች ለእውነተኛው የአኅጉሪቱ እድገት የ'ባለቤትነት' ሚና መጫወት አለባቸው - ሱዳናዊው ተንታኝ
16:10 03.04.2026 (የተሻሻለ: 16:14 03.04.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ባንኮች ለእውነተኛው የአኅጉሪቱ እድገት የ'ባለቤትነት' ሚና መጫወት አለባቸው - ሱዳናዊው ተንታኝ
የግል ባለሀብቶችን፣ የሉዓላዊ ሀብት ፈንዶችን እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ፍላጎት ማመጣጠን፤ አፍሪካዊ የፋይናንስ ስምምነቶች ትክክለኛ ልማት እንዲያመጡ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን በሩሲያ ፋይናንሺያል ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንቲስት ሱዳናዊው ዶክተር መሐመድ ሁሴን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ከባለሙያው የተገኙ ዋና ዋና ነጥቦች፦
🟠 የግል ባለሀብቶች ትርፍ ይፈልጋሉ፣ የሉዓላዊ ሀብት ፈንዶች ስልታዊ ተደራሽነትን ይሻሉ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ደግሞ መረጋጋትን ይፈልጋሉ።
🟠 እንደ አፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ አፍሪኤግዚም ያሉ የአፍሪካ የልማት ባንኮች፣ የግል ካፒታል የአፍሪካን የሂሳብ መዝገብ እንደ "ምቹ የትርፍ ማግኛ ዕድል" ብቻ እንዳይጠቀምበት መከላከል አለባቸው።
🟠 የዕዳ ፋይናንስ ሽግሽግ ጠቃሚ የሚሆነው ለለውጥ የሚሆን ጊዜ የሚገዛ ከሆነ ብቻ እንደሆነ ያስጠነቀቁት ተንታኙ፤ መዋቅራዊ ድክመቶችን ለማራዘም ብቻ የሚደረግ ከሆነ ግን ፋይዳ የለውም ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X