ሞሮኮ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ምክንያት የሚከሰተውን የኢነርጂ ወጪ ጫና ለመቀነስ በየወሩ የ180 ሚሊዮን ዶላር ድጎማ ይፋ አደረገች
15:34 03.04.2026 (የተሻሻለ: 15:44 03.04.2026)
ሰብስክራይብ
ሞሮኮ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ምክንያት የሚከሰተውን የኢነርጂ ወጪ ጫና ለመቀነስ በየወሩ የ180 ሚሊዮን ዶላር ድጎማ ይፋ አደረገች
ሞሮኮ ያዘጋጀችው የአደጋ ጊዜ ዕቅድ ሦስት ዋና ዋና እርምጃዎችን የያዘ መሆኑን የበጀት ሚኒስትሩ ፋውዚ ለክጃ የቻይና የዜና ወኪል በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ የአደጋ ጊዜ ዕቅዱ የሚከተሉትን ያካትታል፡-
የቤት ውስጥ ቡቴን ጋዝ ዋጋን እንዳይጨምር ማገድ፤ ለእያንዳንዱ 12 ኪሎ ግራም ሲሊንደር የ8 ዶላር ድጎማ በማድረግ፣
የቤተሰብ የኤሌክትሪክ ታሪፍ እንዳይጨምር በነበረበት ማቆየት እና
ለማጓጓዣ አገልግሎት ሰጪዎች የቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ መስጠት የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ እንዳይደረግ ለመከላከል ይገኙበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X