ለሩሲያ የዩክሬን ቀውስ መንስኤዎችን ማስወገድ የመሠረታዊ መርህ ጉዳይ ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ
ለሩሲያ የዩክሬን ቀውስ መንስኤዎችን ማስወገድ የመሠረታዊ መርህ ጉዳይ ነው - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ሰርጌ ላቭሮቭ በመግለጫቸው ያነሷቸው ሌሎች ነጥቦች ፦

🟠 ሩሲያ እና ግብፅ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡

🟠 በባህሬን የቀረበው የሆርሙዝ ወሽመጥን የተመለከተ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ረቂቅ ውሳኔ ሃሳብ፣ ለቀውሱ ሰላማዊ መፍትሄ የማግኘት እድልን ያሻሽላል ተብሎ አይታሰብም፡፡

🟠 በፋርስ ባህረ ሰላጤ አካባቢ ግጭቶችን ለማቆም እና ድርድሮችን ለመጀመር መስራት አስፈላጊ ነው፡፡

🟠 ሩሲያ እና ግብፅ በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ቀውስ ላይ ስልታዊ በሆነ መልኩ የተጣጣሙ አቋሞች አሏቸው፡፡

🟠 ሩሲያ እና የአረብ ሀገራት በጎርጎሮሳዊያኑ የ2026 ዓመት መጨረሻ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ጉባኤ ለማካሄድ አቅደዋል፡፡

🟠 አሜሪካ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንድትከፍት ዝም ብላ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን፣ እራሷም ግጭቶችን ማቆም አለባት፡፡

🟠 የሆርሙዝ ወሽመጥን የተመለከተው የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ስለ መከላከያ እርምጃዎች የሚገልጽ አንቀጽ ይዟል፣ ነገር ግን ቀደም ሲል እንዲህ ያሉ ውሳኔዎች ለጥቃት እርምጃዎች ማመቻቻ ሆነው አገልግለዋል፡፡

🟠 የሆርሙዝ ውሳኔ ሃሳብ ድርድሮችን ለማደናቀፍ ወይም በኢራን ላይ የሚፈጸምን ጥቃት ወደኋላ ተመልሶ ሕጋዊ ለማድረግ ሊያገለግል ይችላል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0