በደቡብ ሱዳን ሰላም በማስከበር ተልእኮ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በተለያዩ ግዛቶች የሰብአዊ እርዳታዎችን አደረገ
14:44 03.04.2026 (የተሻሻለ: 14:58 03.04.2026)

ሰብስክራይብ
በደቡብ ሱዳን ሰላም በማስከበር ተልእኮ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በተለያዩ ግዛቶች የሰብአዊ እርዳታዎችን አደረገ
በጃንግሌ ግዛት ተልዕኮውን እየፈፀመ የሚገኘው የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በቦር ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የአስቸኳይ የነፍስ አድን ድጋፍ አድርጓል።
የሰላም አስከባሪው ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሰጥዬ አራጌ፣ ሰላም አስከባሪ ሠራዊቱ፣ በጦርነት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ማኅበረሰቦችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ የአስቸኳይ የነፍስ አድን ሥራዎችን እየሰራ የመጣ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዌስተርን ኢኳቶሪያ ግዛት የሚገኘው የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ በበኩሉ፣ በአካባቢው ለሚገኙ ሦስት ተቋማት በጋራ መጠቀም የሚያስችሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በድጋፍ መልክ አበርክቷል።
ድጋፉን ያስረከቡት የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል እንዳለ እሸቱ፣ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን ረጅም ዘመን ያስቆጠረ የሕዝብ ለህዝብ መልካም ግንኙነት እንዳላቸው መግለፃቸውን መከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ የትስስር ገፁ አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X