ኢትዮጵያ የሚያዚያ ወር የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርነትን ተረከበች

ኢትዮጵያ የሚያዚያ ወር የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርነትን ተረከበች
ኢትዮጵያ የሚያዚያ ወር የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርነትን ተረከበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የሚያዚያ ወር የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ሊቀመንበርነትን ተረከበች

ሃገሪቱ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ምክር ቤቱን ዳግም ከተቀላቀለች በኋላ በሊቀመንበርነት ስትመረጥ የመጀመሪያዋ ሲሆን፣ የምክር ቤቱን አጀንዳዎች በይፋ መምራት ትጀምራለች።

​በሊቀመንበርነት ቆይታዋ በአኅጉራዊ፣ ሰላምና ፀጥታ የሚመለከቱ ሀገር በቀልና ጭብጥ ተኮር በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ የምክር ቤቱን ውይይቶች እንደምትመራ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

​ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ከተመሠረተበት እ.ኤ.አ. 2004 ጀምሮ መሥራች አባል ስትሆን፣ አራት ጊዜ በአባልነት መሳትፏንም ሚኒስትሩ በመግለጫው ገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0