የኢትዮጵያ ለ64 ዓመታት ያገለገልውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ስርዓት ሕግ በአዲሱ "የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ" ተካች

የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ
የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 03.04.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ለ64 ዓመታት ያገለገልውን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ስርዓት ሕግ በአዲሱ "የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃ ሕግ" ተካች

ሕጉ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት የወንጀል ፍርድ ሂደት የተጠርጣሪን እና የተከሳሽን እንዲሁም በወንጀል ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ሰብአዊ መብቶች ለማክበርና ለማስከበር የሕግ የበላይነት በማስፈን የአሰራር ስርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን የምክር ቤቱ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እፀገነት መንግሥቱ ገልጸዋል፡፡

የህዝዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዳስታወቀው የጸደቀው ሕግ፦

​▪ቀልጣፋ የፍትሕ ሥርዓት እና ልዩ የምርመራ ዘዴዎችን ያካትታል።

​▪ለተጎጂዎች የካሣ ክፍያን ሥርዓት ያስይዛል።

​▪ለሴቶች፣ ሕፃናት እና አካል ጉዳተኞች መብት ልዩ ትኩረት ይሰጣል።

​▪ከሕገ-መንግሥቱና ከወንጀል ሕጉ ጋር የተጣጣመ ነው።

▪ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች፣ መርሆች እና እሴቶች ጋር የተስማማ ነው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0