የሀገር ውስጥ የሕክምና ምርቶች ድርሻ በሁለት ዓመት ውስጥ ከ8% ወደ 42 በመቶ አድጓል– የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር

ሰብስክራይብ
የሀገር ውስጥ የሕክምና ምርቶች ድርሻ በሁለት ዓመት ውስጥ ከ8% ወደ 42 በመቶ አድጓል– የጤና ሚኒስትር

አሁን ላይ በኢትዮጵያ ከ25 በላይ ተቋማት በፋርማሲዩቲካል እና በሕክምና አቅርቦት ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ 10ኛውን የኢትዮ ኸልዝ ኤግዚቢሽንና ጉባኤን በይፋ በከፈቱበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ በዚህም በዓመት ምርቶችን ከውጭ ለማስገባት ይወጣ ከነበረው ወጪ ላይ ከ53 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል።


“ከወረርሽኙ በፊት 3 የነበሩት የኦክስጅን አምራች ተቋማት ቁጥር አሁን ላይ 58 ደርሰዋል” ሲሉ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በፊት የነበረው ሀገራዊ የኦክስጅን ምርት አቅርቦት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉንም ጠቁመዋል፡፡


ሆኖም ዘርፉ አሁንም ከውጭ ጥገኝነት ባለመላቀቁና የአምራች ተቋማት አቅም ገና በወጉ ባለመገንባቱ የውስጥ አቅምን ለማሳደግ አምራች ተቋማት ከመንግሥት ጋር በትብብር እንዲሰሩ ዶክተር መቅደስ ጥሪ ማቅረባቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

2ኛውን የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓቶች ዐውደ ርዕይ አካቶ የያዘው 10ኛው የኢትዮ ኸልዝ ኤግዚቢሽንና ጉባኤ እስከ መጋቢት 26፣2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ የተቀረጸው ቪዲዮ በትናንትናው ዕለት የተከፈተውን ዐውደ ርዕይን ያሳያል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0