የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ይፋ አደረገ
ሚኒስቴሩ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።
በአዲሱ መመሪያ መሠረት የነዳጅ የዋጋ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦
ቤንዚን፦ 142.21 ብር
ነጭ ናፍጣ፦ 163.09 ብር
ኬሮሲን (የኩራዝ ናፍጣ)፦ 151.39 ብር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ፦ 163.98 ብር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ፦ 160.68 ብር
የአውሮፕላን ነዳጅ፦ 150.48 ብር
መንግሥት ባሳለፍነው መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ተመሳሳይ የዋጋ ጭማሪ አድርጎ የነበረ ሲሆን የዋጋ ማሻሻያው የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋን መሠረት በማድረግ መወሰኑን አስታውቋል።
በሆርሙዝ ሰርጥ በተፈጠረው መስተጓጎል በግዥ ሂደት ላይ የነበረ ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ አለመቅረቡን ሚኒስቴሩ መግለፁ ይታወቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X