የሉጋንስክ ህዝባዊ ሪፐብሊክ ነጻ መውጣት በዩክሬን የሰላም ንግግር ላይ ሩሲያ ያላትን ጥብቅ ፍላጎት ያሳያል - ተንታኝ
10:09 02.04.2026 (የተሻሻለ: 10:17 02.04.2026)

ሰብስክራይብ
የሉጋንስክ ህዝባዊ ሪፐብሊክ ነጻ መውጣት በዩክሬን የሰላም ንግግር ላይ ሩሲያ ያላትን ጥብቅ ፍላጎት ያሳያል - ተንታኝ
ሩሲያ የሉጋንስክ ህዝባዊ ሪፐብሊክን ነጻ በማውጣት፣ "ከባዶ ወሬና ከፕሮፓጋንዳ ስራ" ውጪ ምንም በማያቀርቡት በዘለንስኪ ላይ ያላትን እምነት ማጣቷን እያጠቆመች ነው ሲሉ "የአርሰናል ኦፍ ዘ ፋዘርላንድ" መጽሔት አዘጋጅና ወታደራዊ ተንታኝ አሌክሲ ሊዮንኮቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
"ሩሲያ በዩክሬን ወታደሮች ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ የደህንነት ቀጣናዋን እያስፋፋች ስትሄድ፣ አዳዲስ ጥብቅ ፍላጎቶቿን ታቀርባለች" ብለዋል።
በመጀመሪያ ለድርድር ከቀረቡት ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ዩክሬን ከዶኔትስክ ህዝባዊ ሪፐብሊክ፣ ከሉጋንስክ ህዝባዊ ሪፐብሊክ እንዲሁም ከኬርሰን እና ዛፖሮዢዬ ክልሎች ኃይሏን እንድታስወጣ የነበረ ቢሆንም፣ የዘለንስኪ አገዛዝ ግን ይህንን ለመፈጸም አልቻለም ሲሉ ጠቁመዋል።
ተንታኙ አክለውም፣ "ሩሲያ የዩክሬንን ጦር በኃይል ያባረረች ሲሆን በሂደቱም ከፍተኛ ኪሳራ አድርሳባቸዋለች" ብለዋል።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ፣ ዘለንስኪ የዩክሬን ጦርን ከዶንባስ ለማስወጣት ዛሬውኑ መወሰን አለበት ማለታቸው፣ ከዚህ ቀደም ለሰላም ድርድር ተይዘው የነበሩ ቅድመ ስምምነቶች "አሁን ላይ በተግባር ህልውናቸው ማክተሙን" በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ተንታኙ አስረድተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዩክሬን እና ምዕራባውያን ደጋፊዎቿ በአሜሪካ እና ኢራን ጦርነት ሳቢያ በደረሰባቸው አስከፊ መዘዝ ክፉኛ ተመትተው በደከሙበት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ሲሉም አብራርተዋል።
በልዩ ወታደራዊ ዘመቻው አካባቢ ያለው ምቹ የአየር ሁኔታ መሬቱን እያደረቀው በመሆኑ፣ የሩሲያ ጥቃት አሁን ከዋና ዋና መንገዶች ባለፈ ወደ ጎንዮሽ እና ወደ ጠላት መስመር ዘልቆ ለመግባት የሚያስችል ጥሩ ሁኔታ መፈጠሩን ባለሙያው ገልፀዋል።
"ይህም የዩክሬንን ታጣቂዎች የጀርባ አጥንት ለመስበር አመቺ ወቅት ነው" ብለዋል።
የሉጋንስክ ነጻ መውጣት የሩሲያ የጦር ኃይሎች የልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ሁለት ዋና ዋና ግቦች ማለትም ፦ ትጥቅ ማስፈታት እና ከናዚ አስተሳስብ ማጽዳትን እስኪሳኩ ድረስ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ግስጋሴያቸውን እንዲቀጥሉ ትልቅ ማበረታቻ ይሆናል።
"ጠላት እጁን ለመስጠት ፍቃደኛ ባልሆነበት እና ምዕራባውያን ደጋፊዎቻቸው ዩክሬን ለተጨማሪ ከ2 እስከ 3 ዓመታት መቆየት ትችላለች ብለው በሚያስቡበት በዚህ ወቅት፣ የእኛ ኃይሎች ያንን ቅዠት ለማጥፋት ወደፊት መገስገሳቸውን ይቀጥላሉ" ሲሉ ተንታኙ አጠቃለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X