የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረውን መስተጓጎል ለማካካስ በሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚያደርገውን በረራ እያጠናከረ እንደሚገኝ ገለጸ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈጠረውን መስተጓጎል ለማካካስ በሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚያደርገውን በረራ እያጠናከረ እንደሚገኝ ገለጸ

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፤ የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት የአውሮፕላን ነዳጅ እጥረት በመፍጠር፣ የነዳጅ ዋጋ በማናር እና በቀጣናው በረራዎችን በማስተጓጎል አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሆኖም አየር መንገዱ በነዳጅ አቅርቦት ዙሪያ ከመንግሥት ጋር እየሠራ እንደሚገኝ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

"የነዳጅ አቅርቦት ቀጣይነት እንዲኖረው ከመንግሥት ጋር እየሠራን ነው። የነዳጅ ዋጋ መናርን ለመቋቋም የነዳጅ ወጪ የምንቀንስባቸውን መንገዶች እንፈልጋለን። በተጨማሪም በቀጣናው የነበሩ በረራዎችን ክፍተት አፍሪካን ጨምሮ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ያለንን ትስስር በማጠናከር ለመሸፈን እየሠራን ነው" ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0