- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል።አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ለማስፈር ተይዞ የነበረው ውጥንና የኢትዮጵያ ምላሽ

የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ለማስፈር ተይዞ የነበረው ውጥንና የኢትዮጵያ ምላሽ
ሰብስክራይብ

“እርግጥ ነው፣ ሐሳቡ [የአውሮፓ አይሁዶችን በኢትዮጵያ ማስፈርን] በተመለከተ ለንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የተላከው ደብዳቤ እንግሊዝ እና አሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ነበረው። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግሥት በአንድ አገር ውስጥ ሌላ አገር ለመፍጠር የሚያስችል ይሁንታ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም፤ ምክኛቱም ይህንን መፍቀድ የአገሪቱን ሉዓላዊነት አሳልፎ የሚሰጥ ነውና” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚው ጉዳያችን ወቅታዊውን የመካከልኛው ምስራቅ ሁኔታ መነሻ አድርገን በኢትዮጵያ የቀድሞው ሐረር ጠቅላይ ግዛት የአውሮጳ አይሁዶችን ለማስፈር ተይዞ የነበረው ውጥን እና የኢትዮጵያን ምላሽ ያስቃኘናል። በቀደመው ጊዜ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ቆስጠንጢኖስ በርኸተሰፋ (ዶ/ር) አነጋግረናቸዋል። የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ጤና ባለሙያ እና ምሁር እንዲሁም ተመራማሪ የሆኑትን ኃይሉ ታምሩን (ዶ/ር) አነጋግረን ሰው ሰራሽ አስተውሎ በአፍሪካ የጤና ምርምርን ከማገዝ አንፃር የሚኖረዉን ሚና ቃኝተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0