ኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌሳይን" የተሰኘ ዲጂታል የሰነድ ማረጋገጫ አገልግሎት ይፋ አደረገ

ሰብስክራይብ

ኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌሳይን" የተሰኘ ዲጂታል የሰነድ ማረጋገጫ አገልግሎት ይፋ አደረገ

ኩባንያው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከፍትሕ ሚኒስቴር እና ከፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በመተባበር የዜጎችን እንግልት ይቀንሳል ያለውን አዲስ የቴክኖሎጂ መፍትሄ አስጀምሯል፡፡

በአዲሱ ቴክኖሎጂ መር ሥርዓት፦

በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችና የዲያስፖራ ማኅበረሰብ በአካል ሳይገኙ የውክልና ሥልጣን መስጠትም ሆነ ለማንሳት፣

ድርጅቶችና ዜጎች ማንኛውንም ሕጋዊ ሰነድ ባሉበት ቦታ ሆነው በዲጂታል መንገድ ለማረጋገጥ፣

የጠበቃ ፈቃድ ለማውጣትና ለማደስ የሚያስችል ቀልጣፋ አሠራር ተዘርግቷል።

አገልግሎቱ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የታገዘ የቪዲዮ ማንነት ማረጋገጫው እና ከፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ጋር መቀናጀቱ አስተማማኝ እንደሆነ ኩባንያው አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0