የአፍሪካ ሀገራት የምዕራባውያንን የፖለቲካ አቋም ከዚህ በኋላ ለመከተል ፍቃደኛ እንዳልሆኑ እያሳዩ ነው - ኢትዮጵያዊ የሕግ ምሁር

የአፍሪካ ሀገራት የፖለቲካ አቋም
የአፍሪካ ሀገራት የፖለቲካ አቋም - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.04.2026
ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት የምዕራባውያንን የፖለቲካ አቋም ከዚህ በኋላ ለመከተል ፍቃደኛ እንዳልሆኑ እያሳዩ ነው - ኢትዮጵያዊ የሕግ ምሁር

ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበውን ፀረ-ሩሲያ የውሳኔ ሐሳብ መቃወማቸውን አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየት የሰጡት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው አንዷለም በውቀቱ፤ አኅጉሪቱ በዓለም የጂኦፖለቲካ ጉዳዮች የራሷን ጽኑ አቋም ማንጸባረቅ መጀመሯን ገልጸዋል፡፡


“አፍሪካ ከምዕራባውያን ስብስቦች በመላቀቅ ጥቅሟን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ጽኑ አቋም መያዝ ጀምራለች፡፡ በእኔ አስተያየት አፍሪካ ምዕራባውያን ለማዘዝ የሚሞክሩትን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደለችም። ይህ የሚያሳየው በተለይም የአፍሪካ ሀገራት የምዕራባውያንን የፖለቲካ መመሪያዎች በቀላሉ ለመከተል ፈቃደኛ ያልሆኑበት ባለብዙ ዋልታ ዓለም መፈጠሩን ነው።


የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የምዕራባውያን የፖለቲካ መሳሪያ ነው ያሉት የሕግ ባለሙያው፤ ተቋሙ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ላይ ውጫዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ ሆኖ ማገልገሉን አስታውሰዋል፡፡

ተቋሙ አሁን ምዕራባውያን ስልታዊ ተቀናቃኛችን ናት በሚሏት ሩሲያ ላይ ሙሉ በሙሉ ትኩረቱን እንዳደረገ አንስተዋል፡፡


“ሩሲያን በተመለከተ በተለይም ከ2022 ጀምሮ ከ16 በላይ የውሳኔ ሃሳቦች እንደተሞከሩ ማየት እንችላለን። ይህ ታይቶ የማይታወቅ ቁጥር ነው። እንደኔ ያሉ ታዛቢዎችን የሚያስቆጣው ነገር ኮሚሽኑ በጣም አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውስጥ የሚሳተፉ ሌሎች ሀገራትን እንዳላየ ማለፉ ነው” በማለት አሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም በኢራቅ የፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0