የጤና ሚኒስቴር ለስድስት ክልሎች 12 ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮችና አምቡላንሶችን አበረከተ

ሰብስክራይብ

የጤና ሚኒስቴር ለስድስት ክልሎች 12 ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮችና አምቡላንሶችን አበረከተ

ድጋፉ ለመድረሰ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦችን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

አምቡላንሶቹ የድንገተኛ ጊዜ እንክብካቤ የሚያቀርቡ ሲሆን ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮቹ ደግሞ ቋሚ የጤና ተቋማት በሌሉባቸው ስፍራዎች አስፈላጊውን ሕክምና ይሰጣሉ ተብሏል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የተደረጉት ድጋፎች “ህይወት ለማዳን ተግባራዊ መሳሪያ ሆነው ያገለግላሉ” ብለዋል።

በተለይም የእናቶችና ሕፃናትን ሞት ለመቀነስ እንዲሁም የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው ተመላክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0