ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበውን ፀረ-ሩሲያ የውሳኔ ሐሳብ ተቃወሙ

ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ
ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የቀረበውን ፀረ-ሩሲያ የውሳኔ ሐሳብ ተቃወሙ

በ61ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ከተሳተፉ 49 ሀገራት መካከል 24ቱ በምዕራባውያን ሀገራት የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ውድቅ አድርገዋል።

ፀረ-ሩሲያዊውን የውሳኔ ሐሳብ በመቃወም ድምፅ የሰጡት አራት ሀገራት፤ የአፍሪካ ኅብረት ተለዋጭ ሊቀመንበር የሆነችው ቡሩንዲ፣ ኩባ፣ ቻይና እና ኢትዮጵያ ናቸው። ግብፅ እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ 18 ሀገራት ደግሞ ድምፅ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በየዓመቱ የሚቀርበው ባለ አሥር ገጽ የውሳኔ ሐሳብ፤ የሩሲያን ድርጊት ማውገዝ፣ ወታደሮቿን እንድታስወጣ መጠየቅ እና የዩክሬንን የግዛት አንድነት ማረጋገጥ የሚሉ የተለመዱና እየጠነከሩ የመጡ ይዘቶችን ያካተተ ነው።

የውሳኔ ሐሳቡ በተጨማሪም ሩሲያ አድሏዊ እና ሙሰኛ በማለት ውድቅ የምታደርገው በዩክሬን ጉዳይ ላይ ምርመራ የሚያካሂደውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ኮሚሽንን የሥራ ዘመን ለአንድ ዓመት አራዝሟል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0