ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኒውክሌር ኃይል ልማት ላይ ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታ ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 01.04.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኒውክሌር ኃይል ልማት ላይ ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታ ተፈራረሙ

ስምምነቱ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ ለመጠቀም የምታደርገውን ጉዞ ወደ ተግባር የሚያሸጋግርና የሕግ ማዕቀፎችን መዘርጋት፣ የመሠረተ ልማት ግንባታ እና የሠለጠነ የሰው ኃይል ማፍራትን ያካተተ ነው ተብሏል።

የጋራ ፍኖተ ካርታው የኒውክሌር ፕሮጀክቶችን በተጨባጭ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል ዝርዝር የድርጊት መርኃ-ግብር እንደያዘ የኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ኮሚሽን በማኅበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ልማት ዙሪያ በመስከረም ወር የድርጊት መርኃ-ግብር መፈራረማችው ይታወሳል።

ስምምነቱ የኢትዮጵያን የኃይል ደህንነት ማረጋገጥና ኢኮኖሚያዊ አቅሟን የማጎልበት ዓላማ አለው።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0