https://amh.sputniknews.africa/20260331/3686354.html
ደቡብ አፍሪካ "የሀገሪቱ የንግድ ተቋማት ወደ ኋላ እንዳይቀሩ" ከባለሀብቶች ጋር በቅርበት ትሠራለች - ሚኒስትር
ደቡብ አፍሪካ "የሀገሪቱ የንግድ ተቋማት ወደ ኋላ እንዳይቀሩ" ከባለሀብቶች ጋር በቅርበት ትሠራለች - ሚኒስትር
Sputnik አፍሪካ
ደቡብ አፍሪካ "የሀገሪቱ የንግድ ተቋማት ወደ ኋላ እንዳይቀሩ" ከባለሀብቶች ጋር በቅርበት ትሠራለች - ሚኒስትር በደቡብ አፍሪካ ከተካሄደው የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ሀሳባቸው ያካፈሉት የአነስተኛ ንግዶች ሚኒስትር ስቴላ... 31.03.2026, Sputnik አፍሪካ
2026-03-31T19:48+0300
2026-03-31T19:48+0300
2026-03-31T19:54+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/images/sharing/article/amh/3686354.jpg?1774976043
ደቡብ አፍሪካ "የሀገሪቱ የንግድ ተቋማት ወደ ኋላ እንዳይቀሩ" ከባለሀብቶች ጋር በቅርበት ትሠራለች - ሚኒስትር በደቡብ አፍሪካ ከተካሄደው የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ሀሳባቸው ያካፈሉት የአነስተኛ ንግዶች ሚኒስትር ስቴላ ንዳቤኒ-አብራሃምስ፤ ወደ ሀገሪቱ ስለሚገባው ካፒታል ያላቸውን ተስፋ ሲገልጹ "ተጨማሪ ቢሊዮን ራንዶች... ወደ ሀገራችን እየመጡ ነው" ብለዋል። ይህም አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር መንገድ እንደሚከፍት ጠቁመዋል።መንግሥት የኢንቨስትመንት ተጠቃሚነትን ሁሉን አቀፍ ለማድረግ ከባለሀብቶች ጋር በቅርበት እንደሚሠራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ንዳቤኒ-አብራሃምስ አክለውም የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የመረጃ ማዕከላት፣ የተሻሻለ የኢንተርኔት ተደራሽነት እና የንግድ ተቋማት እርስ በርስ የንግድ ልውውጥ የሚያደርጉባቸውን መድረኮች ጨምሮ በዲጂታል ዕድገት ላይ ትኩረት መደረጉን ገልጸዋል። ይህም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ዘርፉ ውስጥ የሥራ ዕድሎችን ለማስፋፋት ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2026
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
ደቡብ አፍሪካ "የሀገሪቱ የንግድ ተቋማት ወደ ኋላ እንዳይቀሩ" ከባለሀብቶች ጋር በቅርበት ትሠራለች - ሚኒስትር
19:48 31.03.2026 (የተሻሻለ: 19:54 31.03.2026) ደቡብ አፍሪካ "የሀገሪቱ የንግድ ተቋማት ወደ ኋላ እንዳይቀሩ" ከባለሀብቶች ጋር በቅርበት ትሠራለች - ሚኒስትር
በደቡብ አፍሪካ ከተካሄደው የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ሀሳባቸው ያካፈሉት የአነስተኛ ንግዶች ሚኒስትር ስቴላ ንዳቤኒ-አብራሃምስ፤ ወደ ሀገሪቱ ስለሚገባው ካፒታል ያላቸውን ተስፋ ሲገልጹ "ተጨማሪ ቢሊዮን ራንዶች... ወደ ሀገራችን እየመጡ ነው" ብለዋል። ይህም አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር መንገድ እንደሚከፍት ጠቁመዋል።
መንግሥት የኢንቨስትመንት ተጠቃሚነትን ሁሉን አቀፍ ለማድረግ ከባለሀብቶች ጋር በቅርበት እንደሚሠራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ንዳቤኒ-አብራሃምስ አክለውም የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የመረጃ ማዕከላት፣ የተሻሻለ የኢንተርኔት ተደራሽነት እና የንግድ ተቋማት እርስ በርስ የንግድ ልውውጥ የሚያደርጉባቸውን መድረኮች ጨምሮ በዲጂታል ዕድገት ላይ ትኩረት መደረጉን ገልጸዋል። ይህም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ዘርፉ ውስጥ የሥራ ዕድሎችን ለማስፋፋት ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X