የካርግ ደሴትን ለመቆጣጠር መሞከር ለአሜሪካ ጦር 'ራስን ማጥፋት' ይሆናል - ፈረንሳዊ ጸሐፊ
19:42 31.03.2026 (የተሻሻለ: 20:25 31.03.2026)

ሰብስክራይብ
የካርግ ደሴትን ለመቆጣጠር መሞከር ለአሜሪካ ጦር 'ራስን ማጥፋት' ይሆናል - ፈረንሳዊ ጸሐፊ
በደሴቲቱ ላይ የምድር ጦር የማሰማራት ሃሳብን አስመልክቶ ሀሳባቸውን ለስፑትኒክ አፍሪካ የሰጡት ፊሊፕ ሙሬ፤ "ይህ አሜሪካውያን ወታደሮች በኢራናውያን ኢላማ የሚሆኑበት ራስን የማጥፋት ዘመቻ ይሆናል" ሲሉ ተናግረዋል።
"ይህ ደግሞ ፍጹም ስህተት ነው" ሲሉም አቋማቸውን አጋርተዋል።
አሜሪካውያን እና እስራኤላውያን ወታደሮችን መላክ ቢችሉ እንኳ፤ ወታደሮቹ "በኢራናውያን ኢላማ ተደርገው ሰለባ ይሆናሉ" ብለዋል።
መርከቦችን መላክ እጅግ አደገኛ ስለሚሆንም አስፈላጊውን አቅርቦት ማግኘት እንደማይችሉ ገልፀዋል።
አሜሪካውያን በዋናነት ቦምቦችን ለመጣል ቢ-52 የጦር አውሮፕላኖችን ሳያሰማሩ፤ በጦር ጄቶቻቸው ነው የሚሳኤል ጥቃቶችን የሚሰነዝሩት። እነዚህን አውሮፕላኖች ወደ ኢራን መላክ እጅግ አደገኛ ነው ሲሊ ጸሐፊው አጽንኦት ሰጥተዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X