ኢትዮጵያ ካላት የታዳሽ ኃይል አቅም ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው 6.33 በመቶው ብቻ መሆኑ ተገለፀ

ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.03.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ካላት የታዳሽ ኃይል አቅም ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው 6.33 በመቶው ብቻ መሆኑ ተገለፀ

የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ከውኃ፣ ከፀሐይ፣ ከነፋስና ከሌሎች ምንጮች እስከ 150 ጊጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ቢኖራትም እስካሁን የለማው 9.5 ጊጋ ዋት ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህ የተገለጸው በጋሞ ዞን ጋርዳ ማርታ ወረዳ በ500 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በተመረቀበት ወቅት ነው።

ፕሮጀክቱ 710 ኪሎ ዋት ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን 6 ሺህ 500 አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የፀሐይ ኃይል ማመንጫው የአካባቢውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ከማሳለጡ ባለፈ፤ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0