ኢትዮጵያ የመካከለኛውን ምስራቅ ቀውስ ተከትሎ የነዳጅ ቁጠባና የቅድሚያ አሰጣጥ ሥርዓት ዘረጋች
18:29 31.03.2026 (የተሻሻለ: 19:55 31.03.2026)
ሰብስክራይብ
🇪🇹 ኢትዮጵያ የመካከለኛውን ምስራቅ ቀውስ ተከትሎ የነዳጅ ቁጠባና የቅድሚያ አሰጣጥ ሥርዓት ዘረጋች
— Sputnik Ethiopia (@sputnik_ethio) March 31, 2026
⛽️ በሆርሙዝ ሰርጥ በተፈጠረው መስተጓጎል በግዥ ሂደት ላይ የነበረ ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ አለመቅረቡን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር… pic.twitter.com/533moz0Zxn
ኢትዮጵያ የመካከለኛውን ምስራቅ ቀውስ ተከትሎ የነዳጅ ቁጠባና የቅድሚያ አሰጣጥ ሥርዓት ዘረጋች
በሆርሙዝ ሰርጥ በተፈጠረው መስተጓጎል በግዥ ሂደት ላይ የነበረ ከ180 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ነዳጅ አለመቅረቡን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህም መንግሥት ልዩ ክፍል በማቋቋም ከዛሬ መጋቢት 22፣ 2018 ጀምሮ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን እንደሚከታተል ሚኒስትር ካሳሁን ግፌ አስታውቀዋል፡፡
እንደ ሚኒስቴሩ ማብራሪያ፦
▫ ዕለታዊ የናፍጣ አቅርቦት ከ9.2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4.5 ሚሊዮን ሊትር ዝቅ ብሏል።
▫ የዓለም የናፍጣ ዋጋ በአንድ በርሜል ከ80 ዶላር ወደ 230 ዶላር፤ ቤንዚን ደግሞ ከ70 ወደ 150 ዶላር አሻቅቧል።
🟠 ስለሆነም ወቅታዊ ሁኔታውን ታሳቢ በማድረግ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች፣ ላኪ ድርጅቶችና ፋብሪካዎች፣ ትልልቅ የመንግሥትና የግል ፕሮጀክቶች፣ መሠረታዊ ፍጆታ የሚያጓጉዙና የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መመሪያ ተላልፏል።
🟠 ዜጎች ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀሙ፣ አላስፈላጊ ጉዞዎችን እንዲቀንሱ፣ የእግር ጉዞን እንዲያዘወትሩና በሕገ-ወጥ ንግድ ላይ የሚሳተፉትን በማጋለጥ እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X