በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ የዲጂታል ሽግግር እስካሁን 60 የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ አሠራር መጀመራቸው ተገለፀ

የጤና ተቋማት
የጤና ተቋማት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.03.2026
ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ የዲጂታል ሽግግር እስካሁን 60 የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ አሠራር መጀመራቸው ተገለፀ

ይህ ሽግግር ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2030 የጤናውን ዘርፍ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ሥርዓት ለመቀየር የያዘችው ግብ አካል መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ሚኒስቴሩ በጤና ኬላዎችም ጭምር የተለያዩ የዲጂታል አሠራሮችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ገልፀዋል።

ከ30 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የጤና መረጃ ደግሞ በዲጂታል ሥርዓት ተደራጅቶ እንዲያዝ መደረጉን ጠቁመዋል።

የኢንተርኔት ግንኙነት መቆራረጥ፣ የመሠረተ ልማት አቅርቦት እና የሠለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ለዲጂታል ሽግግሩ መሳካት ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ጉዳዮች እንደሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0