የነዳጅ ማደያዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያ እንዲተክሉ ታዘዘ

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያ
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.03.2026
ሰብስክራይብ
የነዳጅ ማደያዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያ እንዲተክሉ ታዘዘ

እርምጃው የነዳጅ ጥገኝነትን ለመቀነስና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አጠቃቀም ለማስፋፋት ያለመ ነው።

ሁሉም ነባር የመኪና መገጣጠሚያዎች ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ምርት እንዲቀየሩ መመሪያ መሰጠቱንና በቀጣይ ዓመታት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መገጣጠሚያዎችን ቁጥር ወደ 60 ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በሪኦ ሀሰን ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል።


"ዘርፉን ይበልጥ ለማስፋፋት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ባለሀብቶች ጋር የአጋርነት ውይይት እየተደረገ ነው" ሲሉም ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል፡፡


መንግሥት የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ዘርፉን ለማበረታታት የታክስ ማቅለያዎችንና ልዩ ልዩ ማበረታቻዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚገኙትን ከ100 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ 500 ሺህ ለማድረስ መታቀዱንም ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0