ኢትዮጵያ ከቻይና አበዳሪዎች ጋር የዕዳ መልሶ ማዋቀር እና ለቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ የገንዘብ ድጋፍ ድርድር አካሄደች
15:24 31.03.2026 (የተሻሻለ: 17:25 31.03.2026)

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከቻይና አበዳሪዎች ጋር የዕዳ መልሶ ማዋቀር እና ለቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ የገንዘብ ድጋፍ ድርድር አካሄደች
በገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ የተመራ የልዑካን ቡድን ከቻይና ኤግዚም ባንክ፣ ከቻይና ልማት ባንክ እና ከኢንዱስትሪና ንግድ ባንክ ጋር የዕዳ ሽግሽግ ሂደት ለማጠናቀቅ ያለመ ስትራቴጂካዊ ውይይት ማካሄዱ ተገልጿል፡፡
ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ አሁን ላይ "የዕዳ ሽግሽግ ድርድሩ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደርሷል" ማለታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል፡፡
ለቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት የሚያስፈልገውን የፋይናንስ ዝግጅት ለማፋጠን ሰፊ ውይይት መካሄዱም ተጠቁሟል፡፡
የቻይና የፋይናንስ ተቋማት ለዕዳ ሽግሽግ ሂደቱ ውጤታማነትና ለኢትዮጵያ ልማት አጋርነታቸውን እንደሚቀጥሉ ዳግም አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X