አፍሪኤግዚም ባንክ ከጋራ አበዳሪዎች በሁለት ምዕራፍ የሚለቀቅ የ2 ቢሊዮን ዶላር ብድር አገኘ

አፍሪኤግዚም ባንክ
አፍሪኤግዚም ባንክ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.03.2026
ሰብስክራይብ
አፍሪኤግዚም ባንክ ከጋራ አበዳሪዎች በሁለት ምዕራፍ የሚለቀቅ የ2 ቢሊዮን ዶላር ብድር አገኘ

ዋና መሥሪያ ቤቱን ካይሮ ያደረገው አበዳሪ ተቋም፤ መጀመሪያ አቅዶ የነበረው 1.5 ቢሊዮን ዶላር ቢሆንም ከባለሀብቶች በቀረበው ከፍተኛ ፍላጎት ምክንያት መጠኑን መጨመሩን በመግለጫው አመልክቷል።


"ይህ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች በባንኩ የብድር ታሪክና ተዓማኒነት ላይ ያላቸውን እምነት በግልጽ የሚያሳይ ነው" ሲሉ የአፍሪኤግዚም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቻንዲ ምዌኔቡንጉ ተናግረዋል።


ባንኩ በዓለም አቀፍ ገበያዎች ዘንድ ያለውን ጠንካራና አስተማማኝ ተደራሽነት እንደሚያጎላም አክለዋል።

የብድር ስምምነቱ ከአውሮፓ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ፣ ከእስያ እና ከአፍሪካ የተውጣጡ 31 አበዳሪ ተቋማትን ያሳተፈ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0