የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋትን ተከትሎ አፍሪካ የዓለም አቀፍ አቅርቦት ሰንሰለትን የመቀየር አቅም አላት — ዛምቢያዊ ባለሙያ

ሰብስክራይብ
የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋትን ተከትሎ አፍሪካ የዓለም አቀፍ አቅርቦት ሰንሰለትን የመቀየር አቅም አላት — ዛምቢያዊ ባለሙያ

በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገችው አፍሪካ አሁን ያለውን ሁኔታ በመጠቀም የራሷን የኢነርጂ አቅርቦት ማረጋገጥ ትችላለች፤ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን በማከማቻ ተቋማት፣ በተጨማሪ የነዳጅ ማጣሪያዎች እና በነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ መዋዕለ ነዋይ ካፈሰሰች ብቻ እንደሆነ የዛምቢያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ሉቢንዳ ሃባዞካ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በተቃራኒው ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከሌሎች አካባቢዎች በሚገባ የነዳጅ ምርት ላይ በከፍተኛው ጥገኛ የሆኑ አንዳንድ ሀገራት በተለይም አውሮፓውያኑ ለከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ሊጋለጡ እንደሚችሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።


"አውሮፓ በቅርቡ መንኮታኮቷ አይቀርም፤ በተለይም ከሩሲያ የሚገቡ የነዳጅ እና የማዳበሪያ ምርቶች ላይ በጣሉት ገደብ ምክንያት ከፍተኛ ችግር ይገጥማቸዋል" ሲሉ ሃባዞካ ገልጸዋል።


የአፍሪካ ሀገራት ግን ወሳኝ የሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶቻቸውን በዕርዳታ ከመለወጥ ይልቅ፤ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ ያላቸውን አቋም ለማጠናከር በኅብረት መደራደር እንዳለባቸው ባለሙያው አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0