“የሐረር ራስ ገዝ የአይሁድ ግዛት" በሶማሊላንድ በኩል የባሕር በር እንዲኖረው ታቅዶ ነበር - ኢትዮጵያዊ ምሁር
19:59 30.03.2026 (የተሻሻለ: 09:15 31.03.2026)

ሰብስክራይብ
“የሐረር ራስ ገዝ የአይሁድ ግዛት" በሶማሊላንድ በኩል የባሕር በር እንዲኖረው ታቅዶ ነበር - ኢትዮጵያዊ ምሁር
እስራኤል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና የሰጠች ሀገረ መንግሥት መሆኗ ከዚህ ዐውድ አኳያ ታሪካዊ አንደምታ አለው ሲሉ የፖሊሲ አማካሪ እና የኢኮኖሚ ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል፡፡
ለመሆኑ “የሀረር ራስ ገዝ የአይሁድ ግዛት" ምንድነው?
ጥር 17፣ 1936 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ እራሱን የሐረር ራስ ገዝ የአይሁድ ግዛት መማክርት ብሎ በሚጠራ አካል አማካኝነት ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የቀረበ ዕቅድ ነው፡፡
የዕቅዱ ዓላማ በናዚ የጀርመን አገዛዝ ጭፍጨፋ ለደረሰባቸው የአውሮፓ አይሁዶች በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ስር የሆነ ራስ ገዝ የአይሁድ አሰተዳደር ሐረር ክፍለ ሀገር ውስጥ ማቋቋም ነበር፡፡
የዕቅዱ ቁልፍ አካል ደግሞ የባሕር በር ሲሆን ይህም በወቅቱ የብሪታኒያ የቅኝ ግዛት አካል ከነበረችው ሶማሊላንድ ጋር በማገናኘት የወደብ ባለቤት የማድረግ ውጥን ነበር፡፡
እንደ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ገለጻ፤ ምክር ቤቱ ሐረርን እና ሶማሊላንድን የመቀላቀል ዕቅድ ነበረው፡፡
“ሐረርን እና ሶማሌላንድን ማዋሃድ ይፈልጉ ነበር። ይህሞ ከ60,000 እስከ 70,000 ካሬ ማይል የሚደርስ መሬት ይሸፍናል። የሐረር ምክር ቤት በግልጽ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ነፃነት ጠይቋል። በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ስር ሆኖ በተመረጠ የአይሁድ አካል ራሱን የሚያስተዳድር ግዛት ይሆን ነበር፡፡”
ሶማሊላንድ እ.አ.አ 1960 ለአጭር ግዜም ቢሆን ነጻነቷን ባወጀችበት ወቅት ቀድማ እውቅና የሰጠችውም እስራኤል እንደነበረች ባለሙያው አስታወሰዋል፡፡
“እስራኤል አሁን እያለች ያለችው ለሶማሊላንድ ቀድመን እውቅና ሰጥተናል፡፡ ሶማሊላንድ ለ30 ዓመታት ዲሞክራሲያዊ እና የተረጋጋች ሀገር ሆና ቆይታለች። ስለዚህ እውቅና እንሰጣታለን ነው።”
አጼ ኃይለ ሥላሴ በወኪላቸው ብላታ ኤፍሬም ተወልደ መድህን በኩል "...የሀገሪቱን ትልቅ ጠቅላይ ግዛት ከሌላ ሀገር ለሚመጣ ቡድን መስጠት አንችልም" የሚል መልስ ሰጥተው ጥያቄውን ውድቅ እንዳደረጉ ታሪካዊ ሰነዶች ያስያሉ።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X