"የእን ታሪክ ማንም አይጽፍልንም" - ኮትዲቯራዊ የፖለቲካ ምሁር
ጋና የአትላንቲክ ባርያ ንግድ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ እጅግ አስከፊው የሰው ልጅ መብት ጥሰት ተደርጎ እንዲፈረጅ ያደረገችውን ጥረት አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየት የሰጡት አንድሬ ሲልቨር ኮናን፤ "አፍሪካ የራሷን ታሪክ መልሳ መጨበጥ አለባት" ብለዋል።
ውሳኔው መጋቢት 16 ቀን በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።
"በሚያሳዝን ሁኔታ በአፍሪካ ብዙ ሰዎች የውክልና ጦርነትን ይመርጣሉ" ሲሉም ተችተዋል።
አፍሪካ ስለ ጀግኖቿ ዘጋቢ ፊልሞችን ባለመስራት ዳተኝነት እንዳለባት ሲናገሩ፤ "ጥፋቱ የምዕራባውያን ነው? አይደለም፣ የእኛው ጥፋት ነው" በማለት ወቀሳ ሰንዝረዋል።
"በእውነት የምንነቃበት ጊዜ አሁን ነው" ያሉት ምሁሩ፤ በተለይም "የአሁኑ ዘመን የባርያ ፈንጋዮች አልሞቱም። ዕድሉን ቢያገኙ እነዚህ ሀገራት በድጋሚ ያደርጉታል" ብለዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X